ቦታ ከፋፍሎ ካርታ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

1/ ለመኖሪያ ቤት ቦታ ሲከፋፈል

  •  በመሬት አጠቃቀምና በአካባቢ ልማት ፕላኑ ወይም በከተማው መሪ ፕላን መሰረት ተፈላጊውን ግንባታ ማሰራት መ
  • የሚከፈለው ቦታ ለመኖሪያ የሚየገለግል ከሆነ  ቢያንስ  6ሜትር ስፋት ያለው የመዳረሻ መንገድ ሲኖረው
  • ቦታው በአራት ማእዘን ሲታይ ከ4ቱ አንዱ ወደመንገድ ያለው ጎን 7 ሜትር ከሆነ
  •  የተከፈሉት ቦታዎች ስፋታቸው ከ150 ሜትር ያነሱ ያለመሆን
  •  ይዞታው በእገዳ ወይም በዋስትና ያልተያዘ መሆን
  •  የይዞታ  ህጋዊ የሆነ የማረጋገጫ ካርታ ያለው
  • ቴክኒካዊ አቀማመጣቸውና የቦታው አጠቃቀም ከከተማው ማስትር ፕላን እንዲሁም ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች  ፕላኖች ጋር የማይቃረን መሆን

2/ ለድርጅት ይዞታን ስለመክፈል

  • በመሬት አጠቃቀምና በአካባቢ ፕላን በኢኮ ሲቲ ፕላን  ከሌላው የአካባቢ ፕላን መሰረት ተፈላጊውን ግንባታ ለማሰራት የሚችል ሲሆን
  • ቦታው በቀጥታ ለድርጅት አገልግሎት እንዲውል ሲታሰብ በከተማው ፕላን መሰረት ቢያንስ 10 ሜትር ስፋት ያለው የመዳረሻመንገድ ስፋት ያለው ሲሆን
  • ቦታው በአራት ማእዘን ሲታይ ከአራቱ አንዱ ወደመንገድ ያለው ጎን ከ15 ሜትር ርዝመት ያላነሰ ከሆነ
  • ይዞታው በዋስትናና እገዳ ያልተያዘ ከሆነ
  •  ይዞታ ውህጋዊ የሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ
  • የቦታ ስፋቱ በአካባቢው ፕላን የሚቀበለው ግንባታ  ማሰራት የሚችል ከሆነ ማለትም የቦታው ስፋት
  • ለኢንደስትሪ ከሆነ
    • ለአነስተኛ 500ካሜ በላይ
    • ለመካከለኛ ኢንደስትሪ 1000 ካሜ በላይ
    •  ለከፍተኛ ኢንደስትሪ 2000 ካሜ በላይ 
  • ለትምህርት ተቋማት
    • ለአጸደ ህጻናት 1500 ካሜ
    • አንደኛ ደረጃ 8000 ካሜ በላይ
    • ለሁለተኛ ደረጃ ከ10000 ካሬ ሜትር በላይ መሆን መቻል አለበት
  • ለጤና ተቋማት
    • ለጤና ኬላ  ከ500 ካሜ በላይ
    • ለክሊኒክ ሲሆን ከ1500 ካሜ በላይ
    • ለጤና ጣቢያ ሲሆን ከ2500 ካ ሜ በላይ
  • ለቢዝነስና ልዩ ልዩ ልማቶች ሲሆን
    • ጂ ፕላስ 4 እስከ 350 ካሬ ሜትር በላይ
    • ጂ ፕላስ 5-6 ከ 450 ካሬ ሜትር
    • ጂ ፕላስ 7-8  ከ600 ካሬ ሜትር/ በላይ
    • ጂ ፕላስ 9-10 ከ 800 ካሬ ሜትር/ በላይ
    • ጂ ፕላስ 10 በላይ  ከ10000 ካሬ ሜትር በላይ

ማንኛውም ክፍያ ሲከፈል ወይምሲቀላቀል ከመንግስት እዳ ነጻ መሆን  ለተሰጠው አገልግሎት ተገቢውን ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል  

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.

Scroll to Top